Fana: At a Speed of Life!

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀገራቸው የ2021 ኦሊምፒክን እንደምታስተናግድ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺዴ ሱጋ ሀገራቸው የ2021ዱን ኦሊምፒክ እንደምታስተናግድ ቃል ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዮሺዴ ሱጋ ከዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በመስራት ዕውን ይሆናል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማንኛውንም ጥረት አድርገን ኦሊምፒኩን እናስተናግዳለን ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሺዴ የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤን በመተካት ነበር ባለፈው ወር የተመረጡት፡፡

ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የ2020 ኦሊምፒክ በጃፓን አስተናጋጅነት እንዲካሄድ ቀጠሮ ይዞ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ሆኖም ኮሮና ቫይረስ በደቀነው አደጋ ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ እንዲሸጋገር መወሰኑን ጃፓን ቱደይ በዘገባው አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.