Fana: At a Speed of Life!

የጅግጅጋ ከተማን ለማስፋፋት ለተያዘው እቅድ 760 ሄክታር መሬት ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅግጅጋ ከተማን ለማስፋፋት ለ10 አመት ለተያዘው መሪ እቅድ 760 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡
የጅግጅጋ ከተማ ትኩረት ተነፍጓት የቆየች ቢሆንም÷ ከለውጡ ወዲህ ባለፉት ሶስት አመታት የክልሉ መንግስት የከተማውን እድገት ለማፋጠን በርካታ የልማት ስራዎችን አከናውኗል።
የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደደር ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሻፊ አህመድ ባለፉት ሶስት አመታት በጅግጅጋ ከተማ ለማስገንባት ከታቀደው 28 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ ውስጥ አብዛኛው መጠናቀቁን ጠቁመው÷ ቀሪዎቹ ግንባታቸው በመካሄድ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
የጅግጅጋ ከተማን ለማሳደግ “ጅግጅጋን እንደ ዱባይ እናደርጋለን” በሚል ራእይ የከተማው የ10 አመት መሪ እቅድ መቀረፁን የገለፁት ስራ አስኪያጁ÷ በእቅዱ መሠረት ከተማውን ለማስፋፋት 760 ሄክታር መሬት መዘጋጁቱንም ነው የተናገሩት።
አያይዘውም አዲሱ ጅግጅጋ ከክልሉ ቤተመንግስት በላይ ባለው አካባቢና ለፈኢሳ መንገድ ላይ የሚቋቋም መሆኑን ጠቁመው÷ በአዲስ መልክ የሚቋቋመው የጅግጅጋ ከተማ መንገድን ጨምሮ ሁሉም መሠረተ ልማቶች እንደሚሟላለት ገልፀዋል።
በከተማው በአሁኑ ጊዜ የሚካሄዱ ግንባታዎች እየጨመሩ በመሆኑ በወር በአማካይ ለ385 ቤት ገንቢዎች ፍቃድ እንደሚሰጥም አስረድተዋል።
በከተማው የሚታየውን የቤት እጥረት ለማቃለል የግሉን ዘርፍ ባሳተፈ መልኩ የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመፍታት እየተሰራ ነው ማለታቸውን የሶማሌ ክልል ብዙኃን መገናኛ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.