Fana: At a Speed of Life!

የ’ገበታ ለሀገር’ መርኃ ግብር የሦስቱን መዳረሻዎች ባህላዊ እሴቶች ያሳየ ነው – ጠ/ሚ ፅህፈት ቤት

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. የተካሄደው የ’ገበታ ለሀገር’ መርኃ ግብር የሦስቱን መዳረሻዎች ባህላዊ እሴቶች ያሳየ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ፅህፈት ቤቱ አልባሳት፣ ምግብ፣ ባህላዊ ቁሳቁሶችን ጨምሮ የነበረው ዝግጅት የእያንዳንዱ ስፍራ ልዩ ገጽታ የታየበት መሆኑንም አስታውቋል።

በሁለተኛው የመርኃ ግብሩ ክፍል እያንዳንዱ መዳረሻ ወደ ፊት የሚኖረውን ገጽታ እና እምቅ አቅም በልዩ ልዩ መንገድ አሳይቷልም ነው ያለው።

በወቅቱ የግንባታዎቹ ንድፍ ለዕይታ በሚያመች መንገድ መቅረቡንም አስታውሷል፡፡

በዚህም የሦስቱን መዳረሻዎች ልዩ ልዩ ገጽታ መነሻ በማድረግ ስፍራዎቹ አልባሳት እና ጨርቃ ጨርቅ ለማምረት ያላቸውን አቅም የሚያሳይ የፋሽን ትርዒት እንዲሁም የጎርጎራን፣ ወንጪን እና ኮይሻን ባህላዊ ምግቦች በግብአትነት በመውሰድ የተዘጋጁ ልዩ የምግብ ዓይነቶች መካተታቸውንም ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.