Fana: At a Speed of Life!

የገቢዎች ሚኒስቴር ሀገርን ለማዳን በሚደረገው ርብርብ ስኬታማ አፈጻጸም እያስመዘገበ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር ሀገርን ለማዳን በሚደረገው ርብርብ ውስጥ ከተቋሙ የሚጠበቁ ቁልፍ ተግባራትን በአግባቡ በመወጣት ስኬታማ አፈጻጸም እያስመዘገበ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት 5 ወራት ውስጥ ማስመዝገብ ከሚገባው ውጤት ውስጥ 92 በመቶውን ማሳካት መቻሉን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የሚኒስቴሩ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም አገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊና ቀልጣፋ በማድረግ በበጀት አመቱ የተያዘውን 360 ቢሊየን ብር ግብር የመሰብሰብ እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ ነው ተብሏል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ፊቱን ወደ ሀገሩ አዙሮ ሀገሩን ለማዳን ርብርብ እያደረገ ይገኛልም ተብሏል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር ሀገርን ማዳን የሚጀምረው ተቋሙ የሚጠበቅበትን ስራ በአግባቡ መወጣት ሲችል ነው በማለት ከወትሮው በተለየ የተቋሙ ሰራተኞች ጊዜያቸውን ሰጥተው እየሰሩ ይገኛሉም ነው የተባለው።
ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከራሱ የተሰበሰበው ግብር ተመልሶ የሚገለገልበትና ሀገሩን የሚያሳድግበት መሆኑን በመረዳት ግብርን በአግባቡ በመክፈል እንዲሁም ህገወጥ ድርጊቶችን በማጋለጥ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባም መልዕካታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በዘቢብ ተክላይ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.