Fana: At a Speed of Life!

የገቢዎች ሚንስቴር ከተለያዩ የግል ባንኮች ጋር የኢ ፔይመንትና ኢ ታክስ ስርአት ለመዘርጋት ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚንስቴር ከተለያዩ የግል ባንኮች ጋር የኢ ፔይመንትና ኢ ታክስ ስርአት መዘርጋት የሚያስችል ስምምነት ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል ተፈራርሟል ።
ጊዜዉ የሚጠይቀውን የተሻለ አገልግሎት መስጠት ያስችል ዘንድ ዘመናዊ አሰራርን በመከተል  ግድ እንደሚለው ታመኖበታል።
ከሁለት አመት በፊት ስራውን የጀመረው የገቢዎች ሚንስቴር ከአምስት ባንኮችና ከመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር የኢፔይመንትና የኢታክስ ማስጀመሪያ የሚያበስር ስምምነት አካሄደዋል ።
የኤሌክትሮኒክስ ታክስ ስስርአት ግብር ከፋዮች ወደ ባንክ መሄድ ሳይገባቸዉ ባሉበት ቦታ ሆነዉ በተዘጋጀው የኤሌክትሮኒክስ መንገድ ክፍያቸዉን ለግብር ሰብሳቢዉ መስሪያ ቤት እንደመፈፅሙ የሚያስችላቸዉ ነው፡፡
የገቢና ወጪያቸውን ጭምር በዚሁ የአሰራር ስርአት ፈጣንና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ ለግብር ሰብሳቢዉ ተቋም የሚያሰውቁበት መንገድ ነዉ።
ባለፉት ሁለት አመታት ንግድ ባንክ ብቻ ይህንን አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ አራት የግል የንግድ ባንኮች ስርአቱ ውስጥ መግባታቸው ደንበኞች የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች ሊቀርፍላቸዉ እንደሚችል በፊርማ ስነስርአቱ ላይ ተገልፇል ።
የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጨምሮ ንግድ ባንክ ፣ዳሽን፣አዋሽ ፣ህብረት እና ብርሃን ባንኮች ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር የፊርማ ሰነ ስርአት ያካሄዱ ተቋማት ናቸዉ::
በብስራት መንግስቱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.