Fana: At a Speed of Life!

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከአውሮፓ ህብረት የትብብር ዘርፍ ሀላፊ ጋር በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከአውሮፓ ህብረት የትብብር ዘርፍ ሀላፊ ኤሪክ ሀበር ጋር በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

አቶ አህመድ ሽዴ በአዲስ አበባ ከሚገኙት የአውሮፓ ህብረት የትብብር ዘርፍ ሀላፊ ኤሪክ ሀበር ጋር በትግራይ እየተካሄደ ስላለው የሰብአዊ ድጋፍ እና የመልሶ ግንባታ ስራዎች ገለፃ አድርገዋል ፡፡

ሚኒስትሩ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን የሰብአዊ ድጋፍን አስመልክቶ ስጋት ሊኖረው እንደማይገባና በትግራይ ያለው የፀጥታ ሁኔታም ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሉን አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስትም በብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስተባባሪነት ከአገር ውስጥና ከውጪ የተራድኦ ድርጅቶች ጋር በመተባበር አስቸኳይ የምግብ እርዳታ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች እና የመድሃኑት አቅርቦቶች ለአብዛኛው የትግራይ ክልል አካባቢዎች ተደራሽ እየተደረጉ እንደሆነ አስረድተዋል ፡፡

በስርጭቱም ለሴቶች ፣ ለህፃናት ፣ ለአረጋውያን እና ለአካል ጉዳተኞች ቅድሚያ እንደሚሰጥም አቶ አህመድ አብራርተዋል ፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለው ኢኮኖሚያዊ ትብብርን በማጠናከር ዙሪያ ላይ ውይይት ማካሄዳቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.