Fana: At a Speed of Life!

የገዳ ስርዓት አበርክቶዎች ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የገዳ ስርዓት አበርክቶዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ተካሄደ።

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደው ኮንፈረንስ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የገዳ እና የባህል ኢንስቲቲዩት የተዘጋጀ ነው፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ከበደ ዴሲሳን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩም የገዳ ስርዓት በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ፣ በሰላም እና በአፍሪካ ህዳሴ ላይ በሚኖረው ድርሻ ዙሪያ ምክክር ተደርጓል።

የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ከበደ ዴሲሳ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግርም፥ የገዳ ስርዓት የዴሞክራሲ መሰረት መሆኑን አንስተዋል።

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የገዳ ስርዓት እና ሰላም ትምህርትን እስከ ሶስትኛ ዲግሪ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮም የገዳ ስርዓት እና ሰላም ዘርፍ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የመስጠት እቅድ እንዳለው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጫላ ዋታ አስታውቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.