Fana: At a Speed of Life!

የጉምሩክ ኮሚሽን “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት” ንቅናቄን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረዉን “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት” ሀገራዊ ንቅናቄ መቀላቀሉን ምክትል ኮሚሽነር ሙሉጌታ በየነ ተናግረዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ዛሬ በሁሉም ቅርንጫፎቹ የሚገኙ ሰራተኞቹ በተሳተፉበት መርሀ ግብር ነው የነጩ ፖስታ ጎርፍ ንቅናቄን የተቀላቀለው።

በመርሃ ግብሩ የሚላከው ደብዳቤ ዓላማ የኢትዮጵያዉያንን እዉነታ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማሳወቅ፣ የአሸባሪዉን ህወሓት ቡድን ሀገር የማፍረስ ፍላጎት ማጋለጥ፣ በሰሜን እዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመዉን ግፍ ማመላከት፣ ያስከተለዉን የሕይወትና የንብረት ጉዳት ይፋ ማድረግ እንዲሁም አሸባሪው ቡድን የሚፈፅማቸዉን ኢሰብአዊ ድርጊቶችና የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ለምዕራቡ ዓለም ማሳወቅ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነር ሙሉጌታ ተናግረዋል።

” የ ነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት መርሃ ግብር በተመሳሳይ ሰዓት በሁሉም የጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች መካሄዱ ተገልጿል።

በብስራት መንግስቱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.