Fana: At a Speed of Life!

የጊንጪ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጊንጪ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ፡፡

ላርሰን ኤንድ ቱርቦ በተባለ የህንድ ኩባንያ የተገነባው የጊንጪ ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ገ/እግዝአብሔር የማከፋፈያ ጣቢያው መጠናቀቅ በጊንጭና በዙሪያው የሚገኙ ከተሞችን የኃይል መቆራረጥ ከማስቀረቱም በተጨማሪ ወደ ፊት አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ እንደሚያስችል አስታውቀዋል፡፡

የማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል የሚያገኘው ከገፈርሳ እስከ ጌዲዮን ከተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ሲሆን ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮች ተተክለውለታል፡፡

በ2008 ዓ.ም የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪው 67 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ሲሆን ጣቢያው ሁለት ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ገቢ እና 10 ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ያሉት መሆኑን ከኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ሃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.