Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ መምህራን ትምህርና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 2496 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ መምህራን ትምህርና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሠለጠናቸውን ሁለት ሺህ 496 ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ።

የኮሌጁ ዲን ዶክተር ጋልዋክ ሮን በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት ተማሪዎቹ  በመደበኛ፣ ተከታታይና ክረምት መረሐግብር በመምህርነትና  ጤና ሙያ ዘርፎች የሰለጠኑ ናቸው።

ከተመራቂዎቹ መካከል 921 ሴቶች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

ኮሌጁ በክልሉ በመካከለኛ ደረጃ ያለውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ነው የገለጹት ።

የዕለቱ የክብር እንግዳ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ  በበኩላቸው÷ በተለይም የትምህርትና የጤና አገልግሎቱን ለገጠሩ ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ ለተያዘው ግብ መሳካት ኮሌጁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በቀጣይም ኮሌጁ እንደ ክልል ብሎም እንደ ሀገር ጥራት ያለው የትምህርትና ጤና አገለግሎት ተደራሽ ለማድረግ ለተያዘው ግብ መሳካት ጥራቱን የጠበቀ ሥልጠና በመስጠት  ብቃት ያለው የሰው ኃይል በመፍራት ረገድ ጠንከሮ እንዲሰራ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.