Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ  ክልላዊ መንግሥት በመተከል ዞን በንጹኃን ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አወገዘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በንጹኃን ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አወገዘ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በጥፋት ቡድኖች ማንነትን ባነጣጠረ መልኩ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመን ጥቃት በክልሉ መንግስትና ህዝብ ስም አውግዘዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ ባስተላፉት የሀዘን መግለጫ እንዳስታወቁት የሀገር ነቀርሳ ሆኖ የቆየው የህወሓት የጥፋት ቡድን ዳግም ላይመለስ የተወገደ ቢሆንም ባለፉት 27 ዓመት በጠነሰሰው ሴራ ተስፋ ባልቆረጡ ተለላኪዎች ዛሬም አሳዛኝ ድርጊት እየተፈጸመ ነው።

ሰላማዊ ህዝብን በመጨፍጨፍና በማስጨፍጨፍ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲንቀሳቀስ የነበረው የህወሓት የሽብር ቡድን ላይ መንግስት ከወሰደው እርምጃ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያውያን ያሳዩትን አንድነት ለመሸርሸር የሚሰሩ ተላላኪዎች አሁንም አልጠፉም ብለዋል።

በመሆኑም አሁን ላይ የቡድኑ ቅጥረኞች በጉያችን መኖራቸውን በመገንዘብ የህወሓት ቡድንን ለማስወገድ የታየውን አንድነት በማስቀጠል ቅጥረኞችን ለህግ እንዲቀርቡ የማድረግ ስራ በቁርጠኝነት መስራት አለብን ሲሉም በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

በመተከል ዞን ቡሌን ወረዳ የተፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊት ሰው የመሆን ስብዕና የጎደላቸው ቡድኖች የመፈሙት አፀያፊ ተግባር ለዘመናት የቆየውን የኢትዮጵያዊያን አንድነትና ወንድማማችነት ፈጽሞ ሊሸረሽረው  እንደማይችል አስገንዘበዋል።

“በተለይም በብሔር ላይ ያነጣጠረውን የጥፋት ኃይሎች ጥቃት በጋራ በመመከት ኢትዮጵያ የዜጎች ደህንነት የተረጋገጠባት ሀገር እንድትሆን ሁላችንም በአንድነት ልንሰራ ይገባል” ብለዋል ርዕሰ  መስተዳድሩ።

ርዕሰ መስተዳዳሩ በመግለጫቸው በጥቃቱ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የክልሉ ህዝብና መንግስት ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን በመግለጽ ለሟቾች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን መመኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.