Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልላዊ ምክር ቤት አምስተኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አምስተኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ እንደሚያሂድ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አስታወቁ።

አፈ- ጉባኤው አቶ ጁል ናንጋል ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት የምክር ቤቱ አምስተኛ ምርጫ ስድስተኛ የስራ ዘመን አምስተኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል።

አስቸኳይ ጉባኤው በሚኖረው የአንድ ቀን ቆይታ በየእርከኑ የሚገኙ የምክር ቤት አባላት ብዛት ለመሰወን በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት በማድረግ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃልም ብለዋል።

በጉባኤው ላይ የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ከ250 በላይ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀት ተወካዮች እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.