Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ወጣት የሴራ ፖለቲካ አራማጆችን በዝምታ አይመለከቱም –  የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሰብሳቢ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ወጣት የሴራ ፖለቲካ አራማጆችን በዝምታ አይመለከቱም ሲል የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሰብሳቢ ወጣት ራች ጎች ገለጸ።

የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የውይይት መድረክ ትናንት ተካሂዷል።

ከአሁን በፊት በነበረው የፖለቲካ ሴራ ወጣቱም ሆነ መላው የክልሉ ህዝብ ተጠቃሚ ሳይሆን ቆይቷል ያለው ሰብሳቢው ይህንን የህዝብ ጥቅም የማያረጋግጥ የፖለቲካ ሴራ አካሄድ የክልሉ ወጣት እንደማይቀበለው ገልጿል።

የክልሉ ህዝብ እኩል ተጠቃሚ የመሆን ዕድል ማግኘቱን አስታውሶ፤ “በቀጣይ የሴራ ፖለቲካ አራማጆችን ወጣቱ በዝምታ አይመለከትም” ብሏል።

የሊጉ ምክትል ሰብሳቢ ወጣት ኡጁሉ ቢሩ በበኩሉ “ከአሁን በጎጥና በመንደር በመከፋፈል አንድነቱን ለመሸርሽር ሲሰራ ነበር” ብሏል።

ህዝቡ ልዩነቶች እንዳማያስፈልጉ በመረዳቱ በክልሉ ሰላም መረጋገጡን ጠቅሶ፤ “በቀጣይ በሚስማሙና በሚያግባቡ ጎዳዮች ዙሪያ እንሰራለን” ሲል ተናግሯል።

የመድረኩ ተሳታፊ ወጣቶችም ሀገርን ማልማትና ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ በመግለጽ ሐሳብ አንስተዋል።

ለዘንድሮ ምርጫ ሰላማዊ ሂደትና ለተጀመረው የብልጽግና ጉዞ ስኬታማነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

ከጽንፈኝነትና ከብሄርተኝነት አስተሳሰቦች በመውጣት መንግስት በጀመራቸው የሰላም፣ የዴምክራሲና የልማት ስራዎች በንቃት ለመሳተፍ ዝግጁ እንደሆኑ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ላክደር ላክባክ ፤ በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥና የብልፅግና ጉዞ እውን ለማድረግ ወጣቱ ኃይል የማይተካ  ሚና አለው ብለዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.