Fana: At a Speed of Life!

የጌዴኦ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት መለወጫ በዓል ዳራሮ በዞኑ ቡሌ ወረዳ ተከብሮ ዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የጌዴኦ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት መለወጫ በዓል ዳራሮ በዞኑ ቡሌ ወረዳ ከ525 የጌዲኦበሶንጎዎች ዉስጥ በአንጋፋዉ ሶንጎ ኦዳ ያዓ ሶንጎ ተከብሮ ዉሏል።
በዓሉ የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶች የሚተላለፍበት ነው ተብሏል።
የደራሮ በዓል የጌዴኦ ብሄረሰብ ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲስ ዘመን ስለመሸጋገራቸዉ ማብሰሪያ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የጌዲኦ ብሔር ዘመን መለወጫ ደራሮ በየአመቱ እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ የሚከበር ሲሆን አሁን የሰበሰብነዉ ምርት ይበርክትልን፣ ጤናን ይጠን በሚል የሚከበር ነዉ።
የደራሮ በዓል የጌዴኦ ብሄረሰብ ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲስ ዘመን ስለመሸጋገራቸዉ ማብሰሪያ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ህዝቡ ለአባ ገዳዉ ስጦታ ይዞ በመምጣት ምርቃት የሚቀበልበት በዓል መሆኑ ተመላክቷል።
በበዓሉ ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ፥ ደራሮ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገበብ በ2022 በሩሲያ በሚካሄደዉ የዩኔስኮ ጉባኤ ላይ ይቀርባል ብለዋል።
ለዚህ ደግሞ የተቋሙ አጥኚዎች በቦታዉ በመምጣት የሚያስፈልገዉን መረጃ ሁሉ ሰብስበዉ እንደሄዱ ተናግረዋል።
በዓሉ በዞን ደረጃ እስከ ጥር 28 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚከበር ከዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገልጿል።
በበዓሉ የጌዴኦ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ዝናቡ ወልዴን ጨምሮ የዞንና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በቢቂላ ቱፋና ጌታቸዉ ሙለታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.