Fana: At a Speed of Life!

የግል መገናኛ ብዙኃን ለህብረተሰቡ መረጃ ከመስጠት ባለፈ ማህበራዊ ሀላፊነታቸዉን እየተወጡ ነው – የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግል መገናኛ ብዙኃን ተቋማት በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ምክንያት በአማራና በአፋር ክልሎች ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የዓይነት ድጋፍ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ድጋፉ ለህፃናት የሚውሉ አልሚ ምግቦች፣ ብርድ ልብሶችና ሌሎች ቁሳቁሶችን ያካተተ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
የኢትዮጵያ መገናኝ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ÷ መገናኛ ብዙኃኑ የሀሰት ፕሮፖጋንዳን ከማክሸፍና እውነታውን ለዓለም ከማሳወቅ በተጨማሪ ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን ለመወጣት ድጋፉ ማድረጋቸው የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ጨምሮ 14 የግል (የንግድ) መገናኛ ብዙኃን ናቸው 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የዓይነት ድጋፍ ያደረጉት፡፡
መገናኛ ብዙኃኑ በብሮድካስተሮች ዘርፍ ማህበራት አስተባባሪነት ድጋፉን ያደረጉ ሲሆን÷ የሚደረገዉ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የመገናኛ ብዙኃኑ የስራ ሀላፊዎች ተናግረዋል።
በአዳነች አበበ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.