Fana: At a Speed of Life!

የግብርናውን ዘርፍ በቀጣይ ማዘመን የሚያስችል ስትራቴጂክ አማራጭ ጥናት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግብርናውን ዘርፍ በቀጣይ ማዘመን የሚያስችል ስትራቴጂክ የአማራጭ ጥናት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆነ።

ጥናቱን የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነው ያካሄዱት።

ይህ ጥናት በተለያየ ጊዜ በኮርፖሬሽኑ የስራ አመራሮች የተገመገመ ሲሆን፥ በዛሬው ዕለትም በፌደራል እና በክልል የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገምግሞ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተጠቁሟል።

የቀጣይ ስትራቴጂክ አማራጭ ጥናቱ፥ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና የኮርፖሬሽኑን ውስን ሃብትና ጉልበት እንዲሁም የትኩረት አቅጣጫ ጠቃሚ በሆነ የስራ መስክ ላይ ለማዋል ያለመ ነው ተብሏል።

እንዲሁም ቀጣይ የኢንቨስትመንት ስራዎችን ማህበራዊ ጠቀሜታ ባለው መልኩ ለማከናወን እንዲቻል አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ተነግሯል።

ከዚህ በተጨማሪም በሃገሪቱ የተጀመረውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሚመጥን ደረጃ ሃላፊነቱን በመወጣት ተገቢውን አስተዋጽኦ ለማድረግ እና ለበርካታ ሰራተኞች ዘላቂ የስራ እድል ለመፍጠር የሚያስችል ጥናት መሆኑም ተነስቷል።

በይስማው አደራው

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.