Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ለተፈናቃዮች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአፋር ክልል በህወሓት ጁንታ ወረራ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ የምግብ ፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁስና የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን በክልሉ እንስሳት እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ በኩል ለክልሉ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት አስረክበዋል።

የክልሉ እንስሳት እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም መሃመድ እንደገለጹት÷ በክልላችን በተለያዩ አካባቢዎች በህወሓት ጁንታ ወረራ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ የግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ የምግብ ፣ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁስ እና የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል ፡፡

የክልሉ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሁሴን፥ ድጋፉ የተፈናቃዮቹን ችግር መሰረት ያደረገ በመሆኑ ለተፈናቃዮቹ በአግባቡ እናደርሳለን በማለት ለተደረግው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በአሊ ሹምባህሪ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.