Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የአርሶ አደሮችን ሰብል ሰበሰቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ሀዋስ ወረዳ ናኖ ጀዌ ቀበሌ የአርሶ አደሮችን ሰብል ሰብስበዋል፡፡

የፕሮግራሙ አላማ በልማቱ ግንባር እየተደረገ ያለዉን ርብርብ የመደገፍና የአርሶ አደሮች የሰብል አሰባሰቡን ብክነትን በቀነሰ መልኩ እንዲያከናዉኑ እንዲሁም ለበጋ የመስኖ ልማት ስራ ልዩ ትኩረት በመስጠት የፀጥታ ችግር ባለባቸዉ አካባቢዎች የሚኖረዉን የምርት መቀነስ በሚያካክስ መልኩ እንዲሰሩ መልእክት ለማስተላለፍ መሆኑን የእርሻ ልማትና ሆርቲካልቸር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መለስ መኮንን ገልፀዋል፡፡

በዘንድሮዉ የመኸር ሰብል 12 ነጥብ 9 ሚሊየን ሄክታር በተለያዩ ሰብሎች ተሸፍኖ 374 ነጥብ 66 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ ሲሆን ÷ እስካሁን ባለዉ የምርት አሰባሰብ ሂደት 30 በመቶ የሚሆነው መሰብሰቡን ሚኒስትር ዴኤታዉ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ 70 በመቶ ሰብልን ለመሰብሰብ ለሜካናይዜሽን የሚመቹ አካባቢዎች ላይ የማጨጃና መውቅያ ማሽኖችን በመጠቀም እና በሌሎች ቦታዎች የአርሶ አደሩን ቤተሰብ፣ ተማሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞችን በማስተባበር ብክነት በቀነሰ መልኩ መሰብሰብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ላይ ምዕራባውያን የሚያደርጉትን ጫና በመቃወም የ #በቃ ንቅናቄን ተቀላቅለው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.