Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስትሩ ከአልቪማ ፉድ ኮምፕሌክ ባለቤት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን በኢትዮጵያ ፓስታን በማምረት ወደ ውጭ ከሚልኩት የጂቡቲው ባለሀብት አቶ ዲሬ አሊ ጋር ተወያዩ።
ባለሀብቱ የአልቪማ ፉድ ኮምፕሌክ ባለቤት ሲሆኑ በኢትዮጵያ መዋዕለ-ነዋያቸውን በማፍሰስ ከሃገር ውስጥ ፍጆታ በማለፍ ለጂቡቲ እና ሶማሌላንድ የፓስታ ምርቶችን በመላክ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ላይ እንደሚገኙም ነው የተገለጸው።
ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያውያን የስራ ዕድል በመፍጠር፣ ከውጭ የሚገቡ የፓስታ ምርቶችን በመተካትና የውጭ ምንዛሬን በማስገባት ባለሃብቱ እየተጫወቱ ለሚገኘው ሚና አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
አያይዘውም የጂቡቲ-ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትን በተለይም በምግብና ግብርና ምርቶች-ማቀነባበሪያ ዘርፎች ይበልጥ ለማበረታታት ሁለቱ ሃገራት ተቀራርበው እየሰሩ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
ከዚህ ባለፈም መንግስት እንዲህ ዓይነት ባለሃብቶችን ለማበረታታት አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንደሚያደርግ ለባለሃብቱ አረጋግጠውላቸዋል፡፡
አቶ ዲሬ አሊ በበኩላቸው በመንግስት በኩል እየተደረገላቸው የሚገኘውን ድጋፍ አድንቀው÷ በቀጣይ ሊሰሯቸው ያቀዷቸው ሰፋፊ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ላይ የመንግስት ድጋፍ እንደማይለያቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
በ20 ሚሊየን ዶላር መነሻ ካፒታል የተገነባው የዚህ ኩባንያ ስኬት ሌሎች የጂቡቲ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ይበልጥ የሚያበረታታ መሆኑም በውይይቱ ተገልጿል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.