Fana: At a Speed of Life!

የግብፅ ፣ ጆርዳን እና ኢራቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግብፅ፣ ጆርዳን እና ኢራቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቀጠናዊ ጉዳዮች እና በደረሱበት የሶስትዮሽ ስምምነት ዙሪያ በካይሮ መክረዋል።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ ፣ የጆርዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይማን ሳፋዲ ፣ እና የኢራቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፉአድ ሀሴን ናቸው ውይይቱን ያካሄዱት።

የውይይቱ ዓላማ ሶስቱ ሀገራት ባለፈው ነሃሴ ወር በኦማን በደረሱት የሶስትዮሽ ስምምነት ዙሪያ የነበራቸውን ውይይት ለማስቀጠል ነው።

በወቅቱ የተፈራረሙት ስምምነት ትብብራቸውን ለማሳደግ እንዲሁም ሀገራቱ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በልማት፣ በባህል እና በደህንነት ያላቸውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ሺንዋ ዘግቧል።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ ውይይቱ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል የኢኮኖሚ ማሻሻያን ጨምሮ በኢኮኖሚ ትብብር ላይ ያተኮረ ነበር ብለዋል።

ቀጠናዊ ጉዳዮች መገምገማቸውን የተናገሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሶስቱ ሀገራቱ መሪዎች ከተቀመጠው ራዕይ አንፃር ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ መወያየታቸውንም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.