Fana: At a Speed of Life!

የግንባታው ኢንዱስትሪ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ የዘርፉ ተዋናዮች ሁሉ በቁጭት ስሜት እንዲነሱ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግንባታ ኢንዱስትሪው የሚጠበቅበትን እንዲወጣ የዘርፉ ተዋናዮች ሁሉ በቁጭት ስሜት እንዲነሱ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ አሳሰቡ፡፡

በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በሙያ ደረጃና ብቃት ምዘና ስርዓት ዝርጋታ ላይ የተዘጋጀውን አገር አቀፍ አውደ ጥናትን ሚኒስትሯ በንግግር ሲከፍቱ፥ የግንባታ ኢንዱስትሪው የሚጠበቅበትን እንዳይወጣ ያደረጉ መሰናክሎችን በቁጭት ስሜት መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል ።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ለውጡን ከማይደግፉ ኃይሎች በተቃጣባት ጥቃት ተገዳ ወደ ጦርነት በመገባቷና በዚህም ምክንያት እጅግ በርካታ መሰረተ ልማቶችና የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት በአስከፊ ሁኔታ መውደማቸውን ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

‘’በአሸባሪውና አገር አፍራሹ ቡድን የወደመውን መሰረተ-ልማት መልሶ ለመገንባትና በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ በማስቀጠል የብልፅግና ጉዟችንን ለማፋጠን የግንባታ ኢንዱስትሪው የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ አምናለሁ’’ ብለዋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ በበኩላቸው፥ የግንባታ ኢንዱስትሪው ለረጅም ዓመታት ሲጠቀምባቸው የነበሩ አሰራሮችን በማሻሻል በኩል የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በጥናት የተለዩ 19 የሙያ ደረጃዎችና የአተገባበር ማኑዋሎችም በኢንዱስትሪው ውስጥ በሚገኙ ስምንት የሙያ ማህበራት ተተችተው ወደተግባር ለመለወጥና የጋራ ሰነድ ለማድረግ አውደጥናቱ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

በዚህ አውደጥናት ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች ተመራማሪዎች፣ የሙያ ማህበራት አመራሮችና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማና የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የተገኙ ሲሆን፥ ሰነዶቹን በጥልቀት እንደሚገመግሙም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.