Fana: At a Speed of Life!

የግዙፍ አልማዞች መፍለቂያዋ ቦትስዋና

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦትስዋና በጥቂት ሳምንታት ልዩነት ውስጥ ሁለተኛው ግዙፍ አልማዝ ተገኝቷል።
1 ሺህ አንድ መቶ ሰባ አራት ካራት የሚመዝነው ይህ ግዙፍ አልማዝ በሃገሪቱ ካሮዊ በተባለው የማእድን ማውጫ የተገኘ ነው።
ከዚሁ የማእድን ማውጫ ከአንድ ሺህ ካራት በላይ ክብደት ያላቸው አልማዞች ሲገኙ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።
የማእድን ማውጫው ባለቤት ሆነው የካናዳው ኩባንያ ሉካራ ዳይመንድ፤ ግዙፍ አልማዝ ተከፋፍሎ ወደ ትንንሽ ጌጣጌጦች እንዲቀየር ይደረጋል ብሏል።
ግዙፉን የከበረ ድንጋይ ለሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሞክግዌትሲ ማሲሲ ያቀረበው ኩባንያው፤ አልማዙ ቦትስዋና የግዙፍ አልማዞች መፍለቂያ መሆኗል ያስመሰከረ ነው ብሏል።
ከ2 አመታት በፊት አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ስምንት ካራት የሚመዝነውና የአለማችን ሁለተኛው ግዙፍ አልማዝ በዚሁ ተመሳይ ስፍራ መገኘቱን ሲ ኤን ኤን በዘገባው አስታውሷል።
በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1905 በደቡብ አፍሪካ የተገኘውና 3 ሺህ አንድ መቶ ስድስት ካራት የሚመዝነው አልማዝ ደግሞ የአለማችን ግዙፉ አልማዝ ተብሎ በታሪክ ተመዝግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.