Fana: At a Speed of Life!

የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን በውጤታማነት ለመተግበር እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ቤቶችን መሰረት ያደረገ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን በውጤታማነት ለመተግበር እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዘርፍ ከዲቪቪ ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር ከፌደራልና ከክልል ትምህርት ቢሮ ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ታምራት ይገዙ እንደገለጹት÷ ትምህርት ቤቶችን መሰረት ያደረገ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን በውጤታማነት ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡
ይህንን ሊተገብር የሚችል ሀይል ለማደራጀት ይህ የምክክር መድረክ መዘጋጀቱንም ገልፀዋል፡፡
የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ሥርዓትን ለማስቀጠል የሚያስችል አሰራርና ስልት ተቀይሶ ክህሎትን መሰረት ያደረገ ትምህርት ለመስጠት ወደ ተግባር ተገብቷልም ብለዋል፡፡
የምክክር መድረኩ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ሥርዓትን ለማስቀጠልና ትምህርት ቤቶችን መሰረት ያደረገ የጎልማሶች ትምህርትን ተግባራዊ ለማድረግ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን የጠቀሱት ደግሞ የዲቪቪ ኢንተርናሽናል ዋና ዳይሬክተር አቶ እሸቱ አባተ ናቸው፡፡
የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትን በትምህርት ቤት ደረጃ ተግባዊ ለማድረግ በየትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህራን እዲኖሩ የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቷል መባሉን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.