Fana: At a Speed of Life!

የጎርጎራ፣ወንጪና የኮይሻ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ተጨማሪ የቱሪዝም ምርትና አገልግሎት እንዲኖራት በማድረግ አለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚጨምር ነው – የኢትዮጵያ የቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎርጎራ፤ወንጪና የኮይሻ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ተጨማሪ የቱሪዝም ምርትና አገልግሎት እንዲኖራት በማድረግ አለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚጨምር መሆኑን የኢትዮጵያ የቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር ገለፀ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የማህበሩ ሶስት አባላት የጎርጎራ፣ወንጪና የኮይሻ የቱሪስት መስህብ ልማት ግንባታ ሲጠናቀቅ ተፈጥሯዊና ባህላዊ እሴቶች በመያዝ ጎብኚን በተለያዩ እንቅስቃሴዎች የሚያሳትፉ በመሆናቸው በኢትዮጵያ የሚኖራቸውን ቆይታ እንዲጨምር ያደርጋል ብለዋል።
ሶስቱ የቱሪስት መስህቦች ወደ አገልግሎት ሲገቡም ለአካባቢው አርሶ አደሮች በርካታ የስራ ዕድልም የሚፈጥር በመሆኑ ሰላማዊ የጎብኝት ፍሰት እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።
የኢትዮጵያ የቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር አባል እና የዘርፉ ባለሙያ አቶ ቢንያም ጸጋዬ እንዳሉት የጎርጎራ ፣ወንጪ እና ኮይሻ ፕሮጀክቶች ስራ ዕድል በመፍጠር ረገድ አነስተኛ እና ከቱሪዝም ዘርፍ እንቅሰቃሴ ጋር የሚዛመዱ የንግድ ስራዎች በመፍጠር አማራጭ የስራ ዕድል በሮችን ይከፍታሉ ።
የአለም አቀፍ ቱሪስት ፋሲሊቴሽን ባለሙያው አቶ ቴዎድሮስ ደርበው ደግሞ ፕሮጀክቶቹ ኢትዮጵያን በቱሪዝሙ ዘርፍ ለአለም የምታቀርበውን ምርት እና አገልግሎት አሳድጎ ተወዳዳሪነትን ከፍ ያደረጋል ብለዋል።
ሌላኛው የዘርፉ ባለሙያ ቢኒያም ታዬ እንደ ጎርጎራ፣ ወንጪና ኮይሻ ያሉ አካባቢዎች እስከሁን ያለመልማት ቱሪስቱን አሳምኖ ለማምጣት ለአስጎብኚ ድርጅቶችና ለዘርፉ ባለሙያዎች ስራ ፈተና ሆኖ መቆየቱን አንስተው አሁን ግን አካባቢዎቹ ወደ ልማት እየገቡ በመሆኑ ለዘርፉ ባለሙያዎች ስራን እንደሚያቀል ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም ፕሮጀክቶቹ ለቀጣይ የቱሪዝም መዳረሻዎች ልማት ተምሳሌታዊ ተደረጎ ሊወሰድ ይገባልም ነው የተባለው።
ከዚህ ባለፈ ከፕሮጀክቶቹ ዲዛይን ጀምሮ በርካታ ሰዎችን እያሳተፈ የሚሄድ በመሆኑ በቀጣይ በቱሪዝም ዘርፍ ያለው የሰው ሀይል ክዕሎት እንዲኖረው በማድረግ ሃገራዊ አቅምን ይገነባል ሲሉ ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡
በበላይ ተስፋዬ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.