Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል 24 የኩላሊት እጥበት ሕክምና መስጫ መሳሪያ ተበረከተለት

አዲስ አበባ፣ህዳር 18፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ተቋማት 24 ለኩላሊት እጥበት የሚውል የሕክምና መሳሪያዎች ለጎንደር ዩኒቨርስቲ አበረከቱ።
ቀደም ሲልም 12 ተመሳሳይ መሳሪያዎች ከካናዳ ድጋፍ መገኘቱን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አሸናፊ ታዘበው ገልጸዋል፡፡
የአሁኑ ድጋፍ በመሳሪያ ብልሽት ምክንያት የሚያጋጥመውን የኩላሊት ሕክምና አሰጣጥ ችግር እንደሚቀርፍም ተገልጿል፡፡
መሳሪያዎቹ ሪፈራል ሆስታሉ አዲስ ለጀመረው የውስጥ ደዌና የሕጻናት ህክምና ሆስፒታል እገዛ እንደሚያደርጉ ዶ/ር አሸናፊ ገልጸው÷ ይህንን ድጋፍ ላደረጉና ላስተባበሩ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የተበረከቱት የኩላሊት እጥበት መሳሪያዎች ዋጋ ሲተመን 11 ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር መሆኑን የሆስፒታሉ የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ዋና ዳይሬክተር አቶ አለምዓቀፍ ዋኘው መናገራቸውን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.