Fana: At a Speed of Life!

የጎፋ ዞን ነዋሪዎችና አመራሮች ወደ ግንባር እንደሚዘምቱ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ነዋሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን አርዓያነት በመከተል በከፍተኛ ተነሳሽነት ወደ ግንባር ለመዝመት መወሰናቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደግንባር ለመዝመት መወሰናቸው ሀገር ወዳድነታቸውንና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ መሆናቸውን የሚያሳይ መሆኑንና የቀደሙ መሪዎቻችን ገድል በመድገማቸው የእርሳቸውን ፈለግ ተከትለን እኛም ልንዘምት ይገባል ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡

በጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ምንም ነገር ከአገር በላይ የለንም ፣ የአገሪቱን ህልውና ለማስጠበቅ በተለያየ ሁኔታ ከመደገፍ ባሻገር ወደ ግንባር በመዝመት ታሪካዊ አሻራቸውን ለማስቀመጥ ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ነዎሪዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር መዝመታቸው በግንባር ላይ እየተዋደቀ ለሚገኙት ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መነሳሳትን እንደሚፈጥርና የሞራል ሰንቅ እንደሚሆንም አብራርተዋል፡፡

ሰራዊቱ ከመሪው ጎን ሆኖ ሲዋጋ እንዴት ድል ማድረግ እንዳለበት ያውቅበታል ያሉት ነዋሪዎቹ፥ እኛም በማንኛውም ሰዓት መከላከያ በሚፈልገው ቦታ ለአገራችን መስዋዕትነት ለመክፍል ዝግጁ ነን ብለዋል።

መላው የኢትዮጵያ ህዝብም የጠቅላይ ሚኒስትሩን አርዓያነት በመከተል ወደ ግንባር ማቅናት ያለበት በመዝመት ሌላው ደግሞ በመደገፍ ለአገሩ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ይገባዋልም ነው ያሉት።

በተለይም የቀድሞ ሰራዊት አባላት ለዚህ ጥሪ ግንባር ቀደም በመሆን ትናንት ለአገራቸው የከፈሉትን መስዋዕትነት ዛሬም መድገም አለባቸው ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በማቴዎስ ፈለቀ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.