Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ‘የመደመር መንገድ’ መፅሃፍ ገበያ ላይ ዋለ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ‘የመደመር መንገድ’ የተሰኘው መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ።

መጽሐፉ፥ የለውጡን ፈለግ እና መደመር ያለፈበትን መንገድ እንደሚዳስስ ተነግሯል።

በብዙ ውጣ ውረዶች አልፎ ዛሬ ላይ የደረሰውን ለውጥ የወለዱ አስተሳሰቦች ምን እንደሆኑ፣ ከጥንስሱ ጀምሮ የሪፎርም ጉዞው ምን እንደሚመስል፣ በሂደት የተፈጠሩ መልካምና ፈታኝ አጋጣሚዎች እንዲሁም ተጓዳኝ ታሪኮችን ይዟልም ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እጽፋቸዋለሁ ብለው ሳይፅፉ ለረጅም ዘመናት የቆዩ ትዝታቸው እና ከጓደኞቻቸው ጋር የተጋሯቸው ወዳጃዊ ሐሳቦች ጭምር በመፅሃፉ እንደተካተቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልፀዋል።

በብዙ ጉዳዮች ላይ የተሻለ ግንዛቤ ይሰጣል የሚል እምነት አለኝም ብለዋል።

ቀደም ሲል ለወጣው መጽሐፍ እንደ ተከታይና አስረጂ ሆኖ እንዲያገለግል ዘርዘርና ሰፋ ብሎ፣ ከመጠነኛ የአጻጻፍ ቅርጽ ለውጥ ጋር የተሰናዳ መጽሐፍ ነው።

መጽሐፉ ከሁለት ዓመት በላይ የሆነ ጊዜ እንደወሰደ ገልፀው የተጀመረበት ወቅት ከዚያኛው የመደመር መጽሐፍ ቢቀድም እንጂ አይዘገይም ብለዋል።

መፅሃፉም በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ተሰናድቶ የኅትመት ሥራው በዛሬው ዕለት ገበያ ላይ ውሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.