Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለ35 ህጻናት የበዓል ስጦታ አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ለተገኙ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለሚያሳድጋቸው 35 ህጻናት የበዓል ስጦታ ተበረከተ፡፡

ስጦታውም ለእያንዳንዳቸው 1 ሺህ ብር፣ የትምህርት ቁሳቁስ፣ የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡

ጽህፈት ቤቱ የማህበረሰቡን ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ከሚፈቱ በርካታ ፕሮጀክቶቹ እና ሥራዎቹ አንዱ ህፃናትን ማሳደግ መሆኑም በመርሃ ግብሩ ተገልጿል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት እና ከተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት እንደተገለጸው፥ ልጆችን ባሉበት መደገፍና ማሳደግ በሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተግባራዊ እየሆነ ሲሆን፥ በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ብቻ 320 ህጻናት ስፖንሰር ተደርገዋል፡፡

ይህ ተግባር ህጻናት ጎዳና ከወጡ በኋላ ሳይሆን ገና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሳሉ ሊተገበር እንደሚገባውም እና ቀጣይነቱ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊረባረብ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.