Fana: At a Speed of Life!

የጠነከረች ኢትዮጵያን ለመገንባት ተቃራኒ ዋልታዎች ላይ የሚንጠለጠሉ ፍላጎቶች መቀራረብ አለባቸው-ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጠነከረች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው የብልጽግና ጉዞ አዎንታዊ ሚና መወጣት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ እንደ ሀገር የጋራ ግብ ከያዝን የሀገራችን ህልውና ጠብቀን የጋራ ድል እንደምንቀዳጅ ምንም ጥርጥር የለውም ብለዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ ሁለት ተቃራኒ ዋልታዎች ላይ የሚንጠለጠሉ ፍላጎቶች መቀራረብ አለባቸው ብለዋል።

እኔ ያልኩት ካልሆነ በሚል ግትርነት የሚደረግ ጉዞ፥ ሀብት፣ ጊዜና ጉልበት ከማባከን ውጭ ምንም ጥቅም አይኖረውም ሲሉም በፅሁፋቸው ላይ በአስፍረዋል፡፡

እንዲሁም አንድ እርምጃ ወደ መሐል ለመቅረብ የማይፈቅድ ፍላጎት እንኳን አንድ ሀገርን ቀርቶ አንድ ቤተሰብን አያቆምም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓተቱ ፍላጎቶቻችን በመግራት ለሀገር ያለንን ፍቅር እናሳይ፤ የጠነከረች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው የብልጽግና ጉዞ አዎንታዊ ሚናችንን እንወጣ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.