Fana: At a Speed of Life!

የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 579 ተማሪዎችን አሰመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዲፕሎማ መርሃግብር በህክምና ሙያ ያሰለጠናቸውን 579 ተማሪዎችን አሰመረቀ።

ኮሌጁ በ14ተኛ ዙር በዲፕሎማ መርሃ ግብር በህክምና ያሰለጠናቸውን 579 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

የኮሌጁ ዲን አቶ ዘመነ ሀብቱ ኮሌጁ በህክም ዘርፍ ብቃት ያላቸውን የህክምና ባለሙያዎች እያሰለጠነ ለጤና ስራው መሻሻል እገዛ እያደረገ ነው ብለዋል።

በ14ተኛ ዙር 579 ተማሪዎችን በሰባት የሙያ ዘርፎች በዲፕሎማ ደረጃ ያስመረቀው ኮሌጁ ሁሉም ተማሪዎች የሙያ በቃት ምዘናን ያለፉ መሆናቸውን ዲኑ ገልጸዋል ።

ኮሌጁ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካባቢ ጤና ሙያ 81 ተማሪዎችን ያስመረቀ መሆኑን የተናገሩት አቶ ዘመነ ኮሌጁን ወደ ዩንቨርስቲ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግሥቱ የክልሉን የጤና ሽፋን ለማሳደግ በተደረገው ጥረት 82 ሆስፒታሎች 864 ጤና ጣቢዎችና 3ሺህ938 የጤና ኬላዎች አገልግሎት በመሰጠት ላይ ናቸው ብለዋል።

በጤናው ዘርፍ የባለሙያዎች ዕጥረት እንዳይኖር በክልሉ 5 የጤና ሳይንስ ኮሌጆች ብቁ የሆኑ የጤና ባለሙያዎችን በማሰልጠን ቁልፍ ተግባር እየፈፀሙ መሆናቸውም ተነግረዋል።

ሀላፊው ለተመራቂዎች በሰጡት የስራ መመሪያ እንደገለፁት በቀጣይ በጤናው ዘርፍ የታቀዱ አጀንዳዎችን ለማሳካት የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎች ሙያዊ ሀላፊነታቸውን እንድትወጡ ሲሉም ጠይቀዋል።

በምናለ አየነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.