Fana: At a Speed of Life!

የጢያ ትክል ድንጋይ የመዳረሻ ስፍራ ጥገና ተጠናቆ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጢያ ትክል ድንጋይ የመዳረሻ ስፍራ ጥገና ተጠናቆ ለጎብኚዎች ክፍት መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከፌዴራል ባህል ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት ነው የተሰራው፡፡

አሲዳማ የሆነውን የአካባቢውን አፈር ቅርሱ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ጠርጎና ቆርጦ የማንሳትና የመቀየር ስራ በማከናወን ቅርሱን ከጉዳት መታደግ መቻሉን ከዚህ ቀደም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የጥገና፣ የጎርፍ ማፋሰሻዎችን የማበጀት፣ የማስዋብና ሌሎች መሠል ስራዎች  ተከናውነውለታል፡፡

የጢያ ትክል ድንጋይ በፈረንጆቹ በ1980 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና እና ባሕል ድርጅት /ዩኔስኮ/ በዓለም አቀፍ ቅርስነት መመዝገቡ ይታወሳል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.