Fana: At a Speed of Life!

የጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.