Fana: At a Speed of Life!

የጣሊያን አስጎብኚ ድርጅት የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻዎች ለማስተዋወቅ እንደሚሰራ ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሮም የኢፌዴሪ ኤምባሲ የኢትዮጵያ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ኤምባሲው በሮም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አካባቢያዊ ቢሮ ጋር በመተባባር የመስህብ ስፍራዎችን ለማስተዋወቅ የሚረዳ የበይነ መረብ ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱም ከ12 በላይ የጣሊያን አስጎብኚ ድርጅት ተወካዮች መሳተፋቸውን ኤምባሲው አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ የተፈጥሮ፣ ታሪካዊ እና ዘመናዊ የጎብኚ መዳረሻዎችን እንዲሁም ዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም የተመለከተ ገለፃ ተደርጓል።

እንዲሁም የአስጎብኚ ድርጅቶቹ በቱር ፓኬጆቻቸው ኢትዮጵያን አካተው እንዲሰሩ ተጠይቀው አወንታዊ ምላሽ ሰጥተዋል ተብሏል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአስጎብኚ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት እና የጎብኚዎችን የተሳለጠ ፍሰትን ለማገዝ እያደረገ ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ ወቅት ተሳታፊዎቹ ብዙ ነገር ማወቅ እንደቻሉ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዘርፉ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያደንቁ እና ወደፊት አብረው መስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.