Fana: At a Speed of Life!

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ዛሬ ይመረቃል

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ቁጥር አንድ የ15ቀን የሙከራ የምርት ጊዜውን በማጠናቀቅ ዛሬ ይመረቃል።
ፋብሪካው በቀን 12 ሺህ ቶን ስኳር ማምረት የሚችል ሲሆን በዓመት 2 ሚለየን 372 ሺህ ቶን ስኳር የማምረት አቅም እንደሚኖረው እና በቀን ከ160 ሺህ ቶን በላይ አገዳ ይፈጫል ተብሏል።
ለፋብሪካው 19 ቢሊየን ብር የተመደበለት ሲሆን ለ80 ሺህ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል፡
በሀገራችን ያለውን የስኳር እጥረት በመቅረፍ ረገድ ከፍተኛ አስዋጾ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
ከበለስ ወንዝ 30 ኪሎ ሜትር በተጠለፈ ውሃ አብዛኛው ማሣ ላይ በመርጨት መስኖ የሚጠጣ የሸንኮራ አገዳ ማሣ ያለው የስኳር ፋብሪካው፥ አሁን ላይ አጠቃላይ የለማ የሸንኮራ አገዳ ማሣ 13 ሺህ 667 ሄክታር ሲሆን ፣ ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት ሲገባ 21 ሺህ ሄክታር አጠቃላይ የሸንኮራ አገዳ ማሣ እንደሚያስፈልገውም ሥራ አስኪያጁ አያይዘው ገልጸዋል።
የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ጣና በለስ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ በአማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ የሚገኝ ነው።
በፀጋ ታሪኩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.