Fana: At a Speed of Life!

የጣፋጭ ምግብ አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ የተጣለው ተደራራቢ ታክስ እንዲነሳ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከአምራቾች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

የስኳርና ጣፋጭ ምግቦች አምራች ኢንዱስትሪዎች 70 በመቶ ተደራራቢ ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ኤክሳይስ ታክስ በመክፈላቸው ምክንያት በተፈጠረባቸው ጫና ከዉድድር ውጭ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

90 በመቶ ያህል አምራች ፋብሪካዎችም በተደራራቢነት በተጣለው ታክስ ምክንያት ከስራ ውጭ እንደሆኑ ነው የተመላከተው፡፡

በመሆኑም አምራች ኢንዱስትሪዎች ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ በገበያ ላይ ለመቆየት ስለሚያዳግት ተደራራቢው ታክስ እንዲነሳ ጠይቀዋል።

ከውይይቱ በኋላ እልባት አግኝተው የተዘጉ ጣፋጭ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአልማዝ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.