Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር ትምህርት ለመጀመር የሚስችል ሁኔታ መኖሩን ሲያረጋጥልን ትምህርት እንጀምራለን – የትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስቴር ትምህርት ለመጀመር የሚስችል ሁኔታ መኖሩን ሲያረጋጥልን ትምህርት እንጀምራለን ሲሉ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ አስታወቁ፡፡

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ያለበት ደረጃ ተገምግሞ ትምህርት ለመጀመር የሚያስችል ሁኔታ መኖሩን የጤና ሚኒስቴር ማረጋግጫ ሲሰጥና መንግስት ውሳኔ ሲያሳልፍ ትምህርት እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ከትምህርት ገበታ ውጪ ያሉ ህፃናት በከፍትኛ ሁኔታ እየተጎዱ በመሆኑ ለእነሱ ቅድሚያ እንደሚሰጥም ነው ያብራሩት፡፡

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ለ6 ወር ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ህፃናት ከዚያ በፊት ለሁለት ዓመታት ያክል ይዘውት የነበረውን እውቀት ሊያሳጣቸው ይችላል፡፡

በዚህ ምክንያት ለህፃናት ቅድሚያ ለመስጠት እቅድ መያዙን ገልጸዋል የትምህርት ሚኒስትሩ፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየውም ህፃናት በኮሮና ቫይረስ የመያዝና የማስተላለፍ ባህሪያቸው ከሌሎቹ ያነሰ በመሆኑ ድርጅቱ የሚያስቀምጣቸውን የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ሙሉ ለሙ በመተግበር ትምህርት ለመጀመር ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

በትምህርት አከፋፈት ዙሪያ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ በተስፋፋባቸው እንደ አዲስ አበባ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ትምህርት በ3 ፈረቃ ለመጀመር እቅድ ተይዟል፡፡

ከትላልቅ ከተሞች ርቀው የሚገኙና የቫይረሱ ስርጭት ስጋት በሌለባቸው አካባቢዎችም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንግዶችን በመተግብር ትምህርት እንደሚጀመር መናገራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.