Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ የህክምና ተቋማትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ነሀሴ 21 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ መደበኛ እና የኮሮና ቫይረስ ህክምና አገልግሎትን አሰጣጥን ጎብኝተዋል።
 
በዕለቱም በዞኑ ከተጎበኙት የህክምና ተቋማት መካከል ደገም ወረዳ የሚገኝው የሃምቡሶ ጤና ጣቢያ፣የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣የፊቼ አጠቃላይ ሆስፒታል እንዲሁም በሙከጡሪ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ማከሚያ ማዕከል ይገኙበታል።
 
የሃምቡሶ ጤና ጣቢያ ባለው አቅም እየሰራ የሚገኝና ያሉበትን ችግሮችን ለመፍታት ይሰራል ተብሏል።
 
ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎቹ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በአበበች ጎበና ካምፓስ የሚገኘውን የኮቪድ19 ምርመራ ማዕከል ጎብኝተዋል ።
 
ማእከሉ በክልሉ ካሉ 14 የመመርመሪያ ማዕካላት አንዱ ሲሆን በዞኑ እና ከሌሎች አካባቢዎች የሚመጡ ናሙናዎችን እየመረመረ እንደሚገኝም ተገልጿል።
 
ማዕከሉ አሁን ላይ በሶስት ፈረቃ በቀን ከ አንድ ሺ በላይ ናሙናዎችን እየመረመረ የሚገኝ ሲሆን ÷ እስካሁን ድረስም በማዕከሉ ከ 10 ሺህ 600 በላይ ናሙናዎች መመርመር ተችሏል ነው የተባለው።
 
በዚሁ ወቅት የጤና ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ÷ ማእከሉ በጥሩ ሁኔታ እየሰራ እንደሆነ ተመልክተናል ብለዋል።
 
በኢትዮጵያ ከሳምንታት በፊት የተጀመረው ሃገር ዓቀፍ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማዕከሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር በማመላከት ረገድ የበኩሉን እየተወጣ ይገኛልም ነው ያሉት።
 
ሚኒስትሯ አክለውም አሁንም እንደሃገር የመመርመር አቅምን ለመጨመር ብዙ እየተሰራ ሲሆን ÷እስካሁንም 50 ማዕካላት ምርመራ እያደረጉ ይገኛሉ ነው ያሉት።
 
ከዚያም በመቀጠል ሃላፊዎቹ የፊቼ አጠቃላይ ሆስፒታል የጨቅላ ሕጻናት ሕክምናን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን ተመልክተዋል።
በዚህም ከዚህ በፊት ለሆስፒታሉ የማስፋፊያ እና የህክምና
መሳሪያዎች ቃል ተገብቶ የነበረ ሲሆን መሳሪያዎቹ ወደ አገልግሎትቢገቡም የማስፋፊያ ስራው አለመሰራቱ ተነስቷል።
 
ይህም በቀጣይ እንዲፈታ ይደረጋል ነው የተባለው ።
 
ዶክተር ሊያ በሙከጡሪ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ማከሚያ ማዕከልን የጎበኙ ሲሆን ÷በማእከሉ ከ100 በላይ ታካሚዎች ገብተው 90 ዎቹ አገግመው መውጣታቸው ተገልጿል።
 
ሚኒስትሯ በአራቱም የጤና ተቋማት ጉብኝታቸው የጤና ባለሙያዎቹ እየሰሩ ላሉት ስራ አመስግነዋል።
 
ሃይማኖት ኢያሱ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.