Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር የላቦራቶሪዎች ግንባታ ማስጀመሪያ የውል ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍና ብድር የጤና ሚኒስቴር የላቦራቶሪዎች ግንባታ ማስጀመሪያ የውል ስምምነት ተፈራረመ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት የአገራችንን የጤና ስርዓት ለማሻሻል ከተቀመጡ አቅጣጫዎች ውስጥ የጤና መሰረተ ልማት ማጠናከር አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ላቦራቶሪዎቹ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ደረጃውን የጠበቀ ላቦራቶሪ ግንባታን ጨምሮ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ፣ በሶማሌ፣ በቤኒሻንጉል ፣ በትግራይ ፣ በአፋርና በጋምቤላ ክልሎች የሚገነቡ ናቸው።
ከዓለም ባንክ የተገኘ ከ7 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ብድር እና የገንዘብ ድጋፍ ለግንባታቸው እንደሚውል የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ይህም የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል አቅም በመገንባትና በማጠናከር ተላላፊ በሽታዎችን በወቅቱ ለመለየት አስተማማኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።
በዛሬው እለት ውል የተገባባቸው በ571 ሚሊየን ብር ወጪ በስድስት ክልሎች ዘጠኝ ላቦራቶሪዎች ግንባታ ፕሮጀክቶች ሲሆኑ እስከ ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆኑም ታውቋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.