Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስትሯ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ 1 ሺህ 441ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው ሕዝበ ሙስሊሙ በረመዳን የጾም ወቅት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ያሳየውን ጥንቃቄ በበዓሉ ወቅትም መድገም እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

የበዓሉን ግብይት ርቀትን በመጠበቅ፣ የፊት ጭምብል በማድረግና የእጅ ንጽህናን በመጠበቅ ኅብረተሰቡ እንዲያከናውንም አሳስበዋል።

በበዓሉ ዕለትም ከቤተሰብ ጋር ማክበር፣ የበሰሉ ምግቦችን መጠቀም እንዲሁም እርድን በተመለከተም ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.