Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓል የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ መወሰኑን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አስታወቀ።

ዩኔስኮ በኮሎምቢያ ቦጎታ በቅርስ ጥበቃ ዙሪያ እያካሄደ ባለው ስብሰባ ነው በኢትዮጵያ የጥምቀት በዓል አከባበር የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ውሳኔ ያሳለፈው።

በዚህ መሰረትም የጥምቀት በዓል ከመስቀል፣ ከገዳ ስርዓትና ፍቼ ጨምበላላ በዓላት በመቀጠል በዩኔስኮ የተመዘገበ አራተኛው የማይዳሰስ ኢትዮጵያዊ የዓለም ቅርስ መሆን ችሏል።

በዓሉ በዩኔስኮ የማይዳሰስ የዓለም ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ የኮሚቴው ዓባል የሆነችው ጅቡቲ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቷን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.