Fana: At a Speed of Life!

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ለመከላከያ ሠራዊት 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ለመከላከያ ሠራዊት ያሰባሰበውን 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አስረከበ፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ሠራዊቱ የፈፀመው ተግባር መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያኮራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

“ሠራዊቱ ላከናወነው የጀግንነት ተግባር ያደረግነው ድጋፍ ያንሰዋል” ብለዋል።

በሰራዊቱ ላይ በህወሐት ጁንታ የተፈጸመው የክህደት ጥቃት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አባላት በእጅጉ ያስቆጣቸው እንደነበርም አስታውሰዋል።

ክህደት የተፈጸመበት ሰራዊት ራሱን አደራጅቶ የህግ ማስከበር ዘመቻውን አጠናቆ ወንጀለኞችን ወደ ማደን ተግባር መግባቱ የሚያኮራ መሆኑን ገልጸው፤ “የወደፊት ልጆቻችን ይማሩበታል” ነው ያሉት።

ማህበሩ ካለው ላይ ቀንሶ ድጋፍ ማድረጉ ለሠራዊቱ ያለውን ክብር ለማሳየት መሆኑን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ዘንድሮ የሚከበረውን 80ኛውን የድል በዓልን ከሠራዊቱ ድል ጋር በማያያዝ በድምቀት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ ሰራዊቱ አብሮ እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ ማህበሩ ከሠራዊቱ ጎን በመቆም ላሳየው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

የሕግ ማስከበር ዘመቻው የመከላከያ ሠራዊቱ የአባቶቹንና የአያቶቹን ጀግንነት የደገመበት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.