Fana: At a Speed of Life!

የጨረቃን የተዛባ ዑደት ተከትሎ በሚከሰት የባህር ከፍታ መጨመር የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል – የናሳ ጥናት

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ስፔስ ኤጀንሲ ናሳ እና ሀዋይ ዩኒቨርሲቲ በትብብር በሰሩት ጥናት እንዳመላከቱት ጨረቃ በራሷ ዛቢያ ላይ የምታደርገው ተፈጥሯዊ ዑደት መዛባትና የአየር ንብረት ለውጥ በፈረንጆቹ 2030 ሊከሰት ለሚችል የጎርፍ አደጋ ስጋት መንስኤ ሊሆን ይችላል ተባለ፡፡

አሜሪካ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተሰራው በዚህ ጥናትም እንደተመላከተው÷ከፍተኛው የጎርፍ መጥለቅለቅ የሚከሰተው በፈረንጆቹ 2030 ሲሆን ክስተቱ ለ አስር ዓመታትም ሊቀጥል እንደሚችል ተተንብይዋል፡፡

የአሜሪካ የባህር እና የከባቢ አየር አስተዳደር እንዳስታወቀው በፈረንጆቹ 2019 በአሜሪካ 600 የሚደርስ የጎርፍ መጥለቅለቅ ሲከሰት ይህ አሃዝ ግን እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ በብዙ እጥፍ ሊጨምር ይችላል ነው የተባለው፡፡

ፊል ቶምሰን የተባለው የሃዋይ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና ዋና የጥናቱ መሪ እንዳመላከተው÷ በጨረቃ ዑደት መዛባት ምክንያት የሚከሰተው ይህ የጎርፍ አደጋ በሀሪኬን ምክንያት ከሚደርሰው ይልቅ በመጠኑ ዝቅተኛ የሆነ ውድመት ሊያስከትል ይችላል፡፡

እንደ ጥናቱ በአሜሪካ በወር ከ 10 እስከ 15 ያህል ጊዜ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ከተከሰተ ተፅዕኖው በንግድ ተቋማት እና በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች (ፓርኪንጎች) ላይ ስለሚበረታ በርካቶች ከስራቸው ሊስተጓጎሉ እንደሚችሉ ተመልክቷል፡፡

የጎርፍ አደጋው ውሃማ በሆኑ የአሜሪካ ዳርቻዎች እንዲሁም እንደ ሃዋይ፣ ጉዋም፣ እና አላስካ ባሉ አካባቢዎች ሊበረታ እንደሚችልም ነው የተገለፀው፡፡

ኢ-መደበኛ የጨረቃ ዑደት አዲስ ክስተት እንዳልሆነና ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 1728 ተከስቶ እንደነበረም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡

ምንጭ÷አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.