Fana: At a Speed of Life!

የጭሮ ከተማ ወጣቶች ለሕልውና ዘመቻው ስኬት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረጉ ነው – የወጣቶች ሊግ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጭሮ ከተማ ወጣቶች ለሕልውና ዘመቻው ስኬት አዲስ ንቅናቄ በማካሄድ ላይ መሆናቸውን የከተማው ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡

የከተማው ወጣቶች የአገራችንን ሉዓላዊነት ለማስከበር በግንባር እየተፋለመ ለሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ሁለገብ ድጋፍ ዙሪያ በዚህ ሳምንት አዲስ ንቅናቄ ጀምረዋል።

የጭሮ ከተማ የወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሮ አብደላ ለኢዜአ እንደገለጹት ÷ የከተማዋ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ለመደገፍ በተጀመረው ንቅናቄ እስካሁን ከ50 ሺህ ብር በላይ አሰባስበዋል፡፡

ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበር በማህበረሰብ ፖሊስ አገልግሎት ተሰማርተው አካባቢያቸውን ከአሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ሰርጎ ገቦች እየጠበቁ ነው ብለዋል፡፡

የከተማው ወጣቶች በመርህ ከተቀመጡት የጠብቅ፣ ዝመት፣ ደግፍ አላማን በማሳካት ላይ አጠናክረው እየሰሩ እንደሚገኙ ኃላፊው አክለዋል፡፡

የከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ መሀመድ እንዳሉት ÷ የከተማው ወጣቶች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ነው።

ከንቅናቄው ተሳታፊዎች አንዱ የሆነው ወጣት ሽኩር መሀመድ ÷ የጭሮ ወጣቶች የሀገርን ህልውና በማስቀጠል ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ አላቸው ብሏል።

ሀገራችን በአሸባሪዎች ከተደቀነባት ወቅታዊ የሕልውና አደጋ መታደግ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት ቢሆንም ከወጣቶች ብዙ ይጠበቅብናል ነው ያለው።

ሀገር ለማፍረስ እኩይ ዓላማ አንግበው የተነሱትን አሸባሪዎቹን ህወሓትና ተላላኪው ሸኔን ዳግም የሀገር ስጋት እንዳይሆኑ እየተደረገ ላለው ትግል ወጣቶች ሁለንተናዊ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩም ጠይቋል፡፡

ወጣት ኢፍቱ መሀመድ በሰጠችው አስተያየት “የጭሮ ወጣቶች የሰላማችን ኃይል የሆነውን መከላከያ ሠራዊት ጎን ለመሰለፍ ሁላችንም በአንድነት መንፈስ ቆመናል” ብላለች፡፡

ወጣቷ የአካባቢን ሰላም በማስፈን ከሚደርሱ የፀጥታ ችግሮች አስቀድሞ ለመከላከል በሚደረገው ጥረትም ሆነ በሕልውና ዘመቻው በሀገር ፍቅር ስሜት እየተሳተፈ መሆኑን ጠቅሳለች።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.