Fana: At a Speed of Life!

የጭነት አግልግሎትን ያቀላጥፋል ተብሎ የታመነለት ‘ዚትራክ’ የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የጭነት አግልግሎትን ያቀላጥፋል የተባለ ‘ዚትራክ’ የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ሆነ፡፡

መተግበሪያው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር  በለጠ ሞላ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛውእና የዚ ትራክ የትራንስፖርት አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር ዋና ስራ አስኪያጅ ዮዲት ደነቀው በተገኙበት ነው ትላንት ይፋ የተደረገው።

መተግበሪያው ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያውያን የለማ ሲሆን፥ በስልክና ኮምፒውተር ላይ በመጫን የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማቀላላጠፍ የሚያግዝ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ የኤሌክትሮኒክ ንግድ በኢትዮጵያ በተሟላ ደረጃ ለመተግበር እንደ ‘ዚትራክ’ ያሉ መተግበሪያዎች ዓይነተኛ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል።

በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የእሴት ሰንሰለት ውስጥ ያሉትን ችግሮች በአሰራር፣ በብቁ የሰው ሃይል፣ በአደረጃጀትና በቴክኖሎጂ መቅረፍ ከተቻለ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማድረግ እንደሚቻልም ተናግረዋል።

በጭነት አገልግሎት ለተሰማሩ አስተላላፊዎች፣ አሸከርካሪዎችና ደንበኞች ስራዎቻቸውን ያቀላጥፋል የተባለው መተግበሪያው ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

‘ዚትራክ’ ሶስት መተግብሪያዎችን የያዘ ሲሆን፥ እርስ በእርሳቸው የሚናበቡ የጭነት አገልግሎት ሰጪውንና ደንበኛውን የሚያገናኙ፣ ጭነቱ የደረሰበትን ቦታና የሚደርስበትን ጊዜ ለመከታተል የሚያስችሉ ናቸውም ነው የተባለው።

ስርዓቱ በተለያዩ ቋንቋዎች አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.