Fana: At a Speed of Life!

የፈረሰውን የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባን ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸው የመከላከያ እና የአማራ ክልል ልዩ ሀይል አባላት ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ በአማራ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ  የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሙሉነሽ አበበን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የምዕራብ እዝ መከላከያ ሆስፒታል እና የልዩ ሀይል የቁስለኞች ማቆያ በመገኘት በትግራይ ክልል በተደረገው የሕግ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸውን የመከላከያ እና የአማራ ክልል ልዩ ሀይል አባላት በመጎብኘት አበረታተዋል፡፡

በሕግ ማስከበር ሀገራዊ ተልዕኮው ወቅት ለደረሰው የአካል ጉዳት ድጋፍ እንዲሆን ለሆስፒታሎቹ የዊልቸር፣ ክራንች እና ዎከር ድጋፍም ተደርጓል፡፡

በተመሳሳይ በተያያዘ ዜናም በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ጀግኖች እና ወላጆቻቸው በጦርነት መስዋት የሆኑባቸው የወታደር ልጆች ይኖሩበት የነበረውና የፈረሰውን የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባን ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ለሀገር የዋሉ ጀግኖች ማግኘት የሚገባቸውን ክብርና ትኩረት ወደጎን በማለት የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባ ከለውጡ በፊት በነበረው ስርዓት አገልግሎት እንዲያቆም በመደረጉ በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ጀግኖች እና ወላጆቻቸው በጦርነት መስዋት የሆኑባቸው የወታደር ልጆች ለሀገር ያበረከቱትን ውለታ የዘነጋ ተግባር ሲፈፀምባቸው ቆይቷል፡፡

በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ጀግኖች እና ወላጆቻቸው በጦርነት መስዋት የሆኑባቸው የወታደር ልጆች ይኖሩበት የነበረውና የፈረሰውን የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባን ለማቋቋም በበጎ ፈቃደኝነት የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባ አደራጅ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱን ብሔራዊ የጀግኖችና የሕፃናት አምባ በጎ አድራጎት ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር ዶክተር አዳሙ አንለይ መናገራውን ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ የጀግኖች እና ህፃናት አምባ መቋቋም ለሀገር ክብር ዘብ በመቆም እስከ ህይወት መስዋዕትነት ለከፈሉና እየከፈሉ ላሉ ጀግኖችና ወላጆቻቸውን መስዋት ላደረጉ የጀግኖች ልጆች ተገቢውን ቦታ እና ክብር መስጠት ያስችላል ተብሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.