Fana: At a Speed of Life!

የፈረንሳይ መንግሥት በአማራ ክልል በጦርነቱ ለወደሙ የጤና ተቋማት ማቋቋሚያ የ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳይ መንግሥት በአማራ ክልል በጦርነቱ ለወደሙ የጤና ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ፡፡

ፕሮጀክቱን ለመተግበር ጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

ፕሮጀክቱ በቀዳሚነት የደሴ ሪፈራል ሆስፒታልን መልሶ የሚያቋቁም ሲሆን በሂደትም ሌሎች በጦርነቱ የተጎዱ የጤና ተቋማትን እንደሚደግፍ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ ገልጸዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም የተደረገው ድጋፍ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል የቀደመ አገልግሎቱን መሥጠት የሚያስችለውን ቁመና እንዲገነባ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

አስፈላጊ የሚባሉ ጥገናዎችና ግብዓት የማሟላት ሥራም እንደሚከናወን ነው ያነሱት ፡፡

በተጨማሪም ሚኒስትሯ የፈረንሳይ መንግስት ኮቪድን በመቆጣጠር ሂደት እገዛ ማድረጉን አንስተው አሁንም በጤናው ዘረፍ እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

በዘቢብ ተክላይ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.