Fana: At a Speed of Life!

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሰራተኞች ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሰራተኞች በ”አረንጓዴ አሻራ” መርሃ ግብር በዛሬው እለት ችግኝ ተክለዋል።

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቀለ ሙለታ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፥ የተቋሙ ጋዜጠኞችና ሰራተኞች የዚህ ትውልድ አካል በመሆናቸው የአረንጓዴ አሻራቸውን ማሳረፍ አለባቸው በሚል ነው የዛሬው ተከላ የተካሄደው ብለዋል።

ዓምናም በተመሳሳይ ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ ላይ መሳተፉን በማስታወስ፤ ዘንድሮም ይህንን ለማስቀጠል ችግኝ ተከላው እየተካሄደ መሆኑን አንስተዋል።

ዋና አላማው ለትውልድ የሚተፍር ነገር ማኖር ነው ያሉት አቶ በቀለ፥ “ከተንከባከብነው፣ ካፀደቅነው እና ለቀጣይ ትውልድ ማሻገር ከተቻለ ትርጉም ያለው ስራ እንደሚሆንም ነው” ያስታወቁት።

ዛሬ ከተተከሉት ውስጥ አንዱ አፕል መሆኑን በማንሳትም፤ አፕል እስከ 200 ዓመት ድረስ ፍሬ የሚሰጥ ተክል መሆኑንና ይህም ለቀጣይ ትውልድ የሚተርፍ ነው ብለዋል።

ይህንን ለማስቀጠል ደግሞ መከታተልና አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አክለው ገልፀዋል።

አቶ በቀለ አክለውም ዓምና በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሰራተኞች ከከተከሉ ችግኞች ውስጥ ግማሽ ያክሉ መጽደቃቸውንም አስታውቀዋል።

በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞችን ለመንከባከብ ከወዲሁ ቡድን ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.