Fana: At a Speed of Life!

የፌስቡክ ኩባንያ ትዊተርና ኢንስታግራም ገጾች በመረጃ መዝባሪዎች ተጠልፈው እንደነበር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2012(ኤፍ ቢ  ሲ) ባሳለፍነው ዓርብ ዕለት የፌስቡክ ኩባንያ ትዊተር እና ኢንስታግራም ገጾች በመረጃ መዝባሪዎች ተጠልፈው እንደነበር ተገልጿል።

ገጾቹ ለተወሰነ ጊዜ “አወር ማይን” በተሰኘ የመረጃ መንታፊዎች ቡድን ቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር ተመላክቷል።

ቡድኑ የፌስቡክን ትዊተር እና ኢንስታግራም ገጾች በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኋላም የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፏል።

በመልዕክታቸውም በስማቸው ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ ቡድናቸው የፌስቡክን የትዊተር ገጽ የመጥለፍ አቅም እንዳለው አስገንዝበዋል።

ፌስቡክ “ከትዊተር በተሻለ የተለያዩ የደህንነት ጥንቃቄዎችን ያደርጋል” ሲሉም ተሳልቀዋል።

ከዚህ ባለፈም በኩባንያው ትዊተር እና ኢንስታግራም ገጾች ላይ የራሳቸውን መለያ ምልክት እና አድራሻ ማስተዋወቃቸው ነው የተገለጸው።

ቡድኑ ገጾችን የጠለፈው በአሁኑ ወቅት ያለው የበይነ መረብ ደህንነት አስተማማኝ አለመሆኑን ለማሳየት ነው ብሏል።

ትዊተር በበኩሉ የጠለፋ ሂደቱ በሶስተኛ ወገን የተከሰተ መሆኑን በመግለጽ፥ ችግሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ መፈታቱን አስታውቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.