Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የአዲስ አባባ የውክልና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለው ከፍተኛ ወረፋ ተገልጋዮችን ለእንግልት የዳረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የአዲስ አባባ የውክልና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለው ከፍተኛ ወረፋ ተገልጋዮችን ለእንግልት የዳረገ ነው።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባደረገው ቅኝት የፌደራል በኤጀንሲው የአዲስ አባባ ቅርንጫፍ በነበረው አገልግሎት አሰጣጥ የውክልና አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ወረፋ ተመልክቷል።

ዛሬ በነበረው ውሎ አገልግሎት አሰጣጡ ለአረጋውያንና አካል ጉዳተኞችን ቅድሚያ ያልሰጠ፣ ለኮቪድ 19 ወረርሽኝም በሚያጋልጥ መልኩ እየተካሄደ መሆኑንም ተመልክቷል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር  አቶ ሙሉቀን አማረ፥ ዛሬ የተከሰተው ወረፋ የውክልና አገልግሎት በርካታ ተገልጋይ መኖሩን ተከትሎ በሰራተኞች ላይ በተፈጠረ የስራ ጫና ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።

በተቋሙ ከዚህ በፊት ለኮቪድ 19 ጥንቃቄ እና ለአረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆኑን አንስተው የታየው ችግር በተፋጠነ ሁኔታ ይስተካከላል ብለዋል።

ተቋሙ አሁን ላይ ከ10 ባንኮች ጋር ሃሰተኛ ሰነዶችን መከላከል የሚያሰችል የውል ማጣሪያ ስርአት የዘረጋ ሲሆን፥ ከቀሪ 8 ባንኮች ጋር ደግሞ የጋራ የማጣሪያ አሰራር ይዘረጋል ብለዋል።

ከአዲስ አባባ ከተማ ወሳኝ ኩነት መዝገባ ጋርም በየቀበሌው የሚወጡ ሃሰተኛ መታወቂያን ማስረቀረት የሚያሰችል የጋራ የማጣሪያና መከታተያ ሰርአት ለመዘርጋት ስምምነት ማደረጋቸውን ገልጸዋል።

ተቋሙ አጠቃላይ 14 ቅርጫፎቸ ያሉት ሲሆን፥ በአሁን ወቅት በሁሉንም ቅርጫፎች የሚሰጠውን አገልግሎት አሰጣጥን እና የተገልጋይ አቅስቃሴ መከታተል የሚያሰችል በካሜራ የታገዘ ስርአት ዘርግቶ ከዋናው ቢሮ ቁጥጥር ማደረግ መጀመሩን ጣቢያቸን በምልክታው ለማየት ችሏል።

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.