Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል የዴሞክራሲ ተቋማት የጋራ ፎረም መተዳደሪያ ድንጋጌ ጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል የዴሞክራሲተቋማት የጋራ ፎረም መተዳደሪያ ድንጋጌ ፀደቀ፡፡
የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ጫላ ለሚ÷ በመተዳደሪያ ድንጋጌው ዝግጅት ላይ ባለድርሻ አካላትና የህግ ባለሙያዎች መሳተፋቸውንና ሰፊ ውይይቶች መደረጉን አብራርተዋል፡፡
መተዳደሪያ ድንጋጌውን ያቀረቡት አቶ ደበበ ወልደጊዮርጊስ ÷ ሰነዱ ከመዘጋጀቱ በፊት በዘጠኝ ነፃና ገለልተኛ ሆነው በሚሰሩና ተጠሪ ተቋማት ከምክር ቤቱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ ተጠያቂነት፣ ለህዝብ ያላቸውን ተደራሽነት፣ የበጀትና የሰው ሀብት አስተዳደራቸው እና ያጋጠማቸውን ችግሮች በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት መደረጉን ገልጸዋል፡፡
አቶ ደበበ አያይዘውም የተዘጋጀው መተዳደሪያ ድንጋጌ የፎረሙ አባላት በመደበኛነት በመገናኘት የጋራ ዕቅድ የሚያወጡበትና የአፈጻፀም ግምገማ እና የምክክርና የልምድ ልውውጥ የሚፈጥሩበትን ምህዳር ይፈጥራልም ብለዋል፡፡
በቀረበው ሰነድ ላይም ከተሳታፊዎች በርከት ያሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን÷ ተቋማቱ ‹‹የዴሞክራሲ ተቋማት›› ከሚባሉ ‹‹ነፃ ወይም ገለልተኛ ተቋማት ቢባሉ›› የሚል ሀሳብ ተነስቷል፡፡
የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ተቋማቱ ነጻና ገለልተኛ ሆነው የሚሰሩ ቢሆንም ተጠሪነታቸው ለምክር ቤቱ በመሆኑ ̎ተጠሪ ተቋማት” በሚል ቢጠሩ አግባብነት እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
የፌደራል ተጠሪ ተቋማት የጋራ ፎረም መተዳደሪያ ድንጋጌንም ለጉባኤ አቅርበው አፀድቀዋል፡፡
በተመሳሳይ ዜናም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እና ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፎርም ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል፡፡
ቦርዱ አንድ አዋጅ እና 29 ማስፈጸሚያ መመሪዎችን ማውጣት፣ የሰው ሀይልን ማደራጀት፣ የምርጫ ቁሳቁሶችን ማሟላት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ እና የህዝብ ግንኙነት ተግባራት በዋናነት ማከናወኑ ተገልጿል፡፡
በተመሳሳይም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፎርም በዋና ኮሚሽነር በዶክተር ዳንኤል በቀለ ቀርቧል፡፡
ዶክተር ዳንኤል ኮሚሽኑ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ ለመስራት የሚያስችለውን የህግ ማዕቀፍ ከማሻሻል ጀምሮ በርካታ ስራዎች እንደሰራ መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.